በአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ሊደረግ ነው
19:42 06.10.2025 (የተሻሻለ: 19:44 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ሊደረግ ነው
ጥናት ሲደረግባቸው የቆዩና በየአካባቢው ያሉ በባሕላዊ መንገድ ግጭት የሚፈታባቸው የሽምግልና ሥርዓቶች በዚህ ዓመት ወደ ተግባር እንደሚገቡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡
ለዚህም አዋጅ መውጣቱንና በቀጣይ ግዜያት ሥራ እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ለሀገር ውስጥ ሚድያ ተናግረዋል፡፡
ፍርድ ቤቶቹ በማህበረሰቡ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከፍተኛ ጠቀሜ እንዳላቸው ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ዕውቅና በመስጠት በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ተግባራዊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
መደበኛ ፍርድ ቤቶች ለሀገራዊ እድገት ጠቀሜታ ያላቸው ተግባራት ላይ በትኩረት እንዲሠሩ እንደሚደረግ ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X