ኢትዮጵያ ምሥራቅ አፍሪካን ወደ ተቀናጀ የቱሪዝም ማዕከልነት ለመቀየር እየሠራች እንደሆነ ገለፀች
19:16 06.10.2025 (የተሻሻለ: 19:24 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ምሥራቅ አፍሪካን ወደ ተቀናጀ የቱሪዝም ማዕከልነት ለመቀየር እየሠራች እንደሆነ ገለፀች
ሀገሪቱ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ ቱሪዝምን ለማጎልበት እንቅስቃሴ መጀመሯን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡
“በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል የጋራ ባሕላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዓዊ መስህቦችን በማገናኘት ቱሪስቶች በአንድ የጉዞ መርሃ-ግብር በርካታ ሀገራትን በቀላሉ እንዲጎበኙ የሚያስችል የተቀናጀ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማቋቋም እየተሠራ ነው” ሲሉ በሚኒስቴሩ የቱሪዝም ማስፋፊያ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ ተክሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያም የቪዛ አሰጣጥ ሂደቶችን ለማፋጠንና በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል ቀጣናዊ የቪዛ ስርዓት እቅድ አዋጭነትን ለመፈተሽ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቁመዋል፡፡
ቀጣናውን የተሳሰረ እና ሁለገብ መዳረሻ አድርጎ በማቅረብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዓለም አቀፍ ተጓዦች በመሳብ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነተን ማጎልበት እንደሚቻል መግለፃቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X