ኬንያ የኢንቨስትመንትና የመሠረተ ልማት ፈንድ ታቋቁማለች - ፕሬዝዳንት ሩቶ
18:50 06.10.2025 (የተሻሻለ: 18:54 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኬንያ የኢንቨስትመንትና የመሠረተ ልማት ፈንድ ታቋቁማለች - ፕሬዝዳንት ሩቶ
እርምጃው የመንግሥት ፋይናንስ ላይ ጫና ያሳደረውን የብድር ክምችት በማስወገድ በቁልፍ ዘርፎች በስትራቴጂካዊ መንገድ ኢንቨስት ለማድረግ ያለመ መሆኑን የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ተናግረዋል፡፡
ይህንን ኢኒሼቲቭ ለመደጎም ሕግ አውጪዎች መንግሥታዊ ንብረቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሂደት የሚመራበትን ሕግ አፅድቀዋል፡፡
ንብረቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ የማዘዋወር ሂደቱ በኬንያና ጎረቤት ሀገራት የነዳጅ አቅርቦት የሚያስተዳድረውን የኬንያ ቧንቧ መስመር ኩባንያ የአክሲዮን ድርሻ በመሸጥ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡ የዚህ አክሲዮን ሽያጭ እስከ 1.01 ቢሊዮን ዶላር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የመሠረተ ልማት ፈንዱ ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የሰብል ምርት በከፍተኛ መጠን በማሳደግ የኬንያን የግብርና ዘርፍ ለማጠናከር ቅድሚያ እንደሚሰጥ ሩቶ ገልፀዋል፡፡ ኬንያ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሸጋገር አሁን ካላት 2 ሺህ 300 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም ላይ 10 ሺ ሜጋዋት ኃይል መጨመር ስለሚያስፈልጋት፤ ፈንዱ የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት ለመጨመር እንደሚውልም ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X