እስራኤልና ሃማስ ስለ ጋዛ በግብፅ የሚያደርጉት ድርድር ቁልፍ ዝርዝር ነጥቦች

እስራኤልና ሃማስ ስለ ጋዛ በግብፅ የሚያደርጉት ድርድር ቁልፍ ዝርዝር ነጥቦች
ጦርነቱ ከተጀመረ ከሁለት ዓመት ወዲህ እጅግ ወሳኙ ድርድር ዛሬ ይካሄዳል፡፡
1⃣ ተሳታፊ ልዑካን
በካህሊል አልሃያ የሚመራው የሃማስ ልዑካን ቡድን እሁድ እለት ሻርም ኤል ሼክ ደርሷል፡፡
በስትራቴጂክ ጉዳዮች ሚኒስትር ሮን ደርመር የሚመራው የእስራኤል ልዑካን ቡድን ዛሬ ግብፅ ይገባል፡፡
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀድሞ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር በድርድሩ ላይ ይሳተፋሉ፡፡
2⃣ የድርድሩ ዐውድ
ውይይቱ ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት ጦርነቱን ለማቆም በይፋ ያቀረቡትን አዲስ እቅድ ተከትሎ የሚካሄድ ነው፡፡
እቅዱ የተኩስ አቁም፣ የእስረኞች ልውውጥ እና በሂደት ሃምስን ትጥቅ ማስፈታት ያካትታል፡፡
ግብፅ፣ ኳታርና አሜሪካ እቅዱ ተግባራዊ የሚሆንበትን አካሄድ ያሸማግላሉ፡፡
3⃣ የተደራዳሪዎቹ አቋም
ቤንያሚን ኔታንያሁ በአሜሪካ የቀረበውን ሀሳብ እንደሚደግፉት ደጋግመው ቢናገሩም የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል በአብዛኛው የጋዛ ክፍል እንድሚቆይ ገልፀዋል፡፡
ሃማስ በአስቸኳይ የእስረኞች ልውውጥና ተኩስ አቁም ዙሪያ በመስማማት ድርድሩን ለመቋጨት ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ ትጥቅ መፍታትን በተመለከተ ሀሳብ ባይሰጥም ሌሎች የፍልስጤም ቡድኖች ግን ፍፁም የማይሆን ነው ብለውታል፡፡ ከእስራኤል ጋር ለሚያደርገው ስምምነት ዓለም አቀፍ ዋስትና እንደሚሻም አስገንዝቧል፡፡
በትራምፕ እቅድ መሠረት ስምምነቱን ማጠናቀቅ ዋነኛ ዓላማ ይሆናል፡፡
ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጆርዳን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር፣ ግብፅ፣ ቱርኪዬ እና ፓኪስታን የሃማስን በጎ አቋም ተቀብለውታል፡፡
4⃣ መሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎች
ከመስከረም 2016 ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በጋዛ ከ67 ሺ በላይ ሞት እና ከ169 ሺ በላይ ጉዳት አስከትሏል፡፡
የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል 1 ሺህ 150 ሞት እና 6 ሺህ 300 ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X