የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም 72 በመቶ ደረሰ
17:56 06.10.2025 (የተሻሻለ: 18:04 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም 72 በመቶ ደረሰ
ግድቡ ሲጠናቀቅ ከሚኖረው 201 ሜትር ከፍታ አሁን ላይ በአማካኝ ከ120 ሜትር በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መብራቱ ተሾመ አስታውቀዋል።
ግንባታው በፋይናንስና ችግር ተጓቶ የነበረ ቢሆንም በተቋሙና በመንግሥት በተወሰዱ እርምጃዎች አሁን የግንባታ ሥራው በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
“በአሁኑ ወቅት የዋናው ግድብ የጥቅጥቅ ኮንክሪት ሙሌት 70 በመቶ፣ የማመንጫ ቤቱ የመጀመሪያ ደረጃ የአርማታ ኮንክሪት 68 በመቶ እንዲሁም የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ መዋቅር ኮንክሪት ሥራ 30 በመቶ ላይ ደርሷል" ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በስፍራው ጉብኝት ላደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አብራርተዋል፡፡
በቀጣይ በኤሌክትሮ ሜካኒካልና ሀይድሮሊክ ስቲል መዋቅር ገጠማ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡ ከጅማ እስከ ጭዳ ባለው መንገድ የሚስተዋለው ችግር ለፕሮጀክቱ የዕቃ ማጓጓዝ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ችግሩ እንዲቀረፍም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X