በፍራፍሬ ጭማቂ አምራቾች ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ግብር ውሳኔ ታገደ
16:41 06.10.2025 (የተሻሻለ: 16:44 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በፍራፍሬ ጭማቂ አምራቾች ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ግብር ውሳኔ ታገደ
የገንዘብ ሚኒስቴር በዘርፉ ባለድርሻ አካላት የቀረበለትን ቅሬታ ተቀብሎ የገቢዎች ባለሥልጣን ከስድስት ዓመታት በፊት በወጣ ደንብ ላይ ተመሥርቶ እንዲከፈል ያዘዘውን ግብር ማስቀረቱን አስታውቋል፡፡
“ከሸማቾች ያልተሰበሰበውን ዕዳ በአምራቾች ላይ መጫን ፍትሐዊ አይደለም “ ብሏል፡፡
አጋጥሞ የነበረው ውዝግብ፦
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የታሸገ መጠጥ፤ የፍራፍሬ ጭማቂ ተብሎ ለመታሰብ ቢያንስ 30 በመቶ የፍራፍሬ ይዘት ሊኖረው ይገባል ብሎ ነበር፡፡
ባለሥልጣኑ ይህንን መስፈርት አያሟሉም ያላቸውን አምራቾች የ4 ዓመት የኋላ ታክስ እንዲከፍሉም ግዴታ ጥሏል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ውሳኔው የሀገር ውስጥ አምራቾችን ሥራ እንዲያቆሙ እንዳስገደደ እና ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ጋር ያላቸውን ተወዳዳሪነት እንደጎዳ በመግለፅ ቅሬታ አቅርቧል፡፡
የቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ የገንዘብ ሚኒስቴር በሕጉ አጻጻፍ ላይ ግልጽነት ተጓድሏል በማለት የገቢዎች ባለሥልጣን ውሳኔን አግዷል።
አምራቾች ምን አሉ?
የኢትዮጵያ መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አሸናፊ መርዕድ፤ “ይህ ለዘርፉ ትልቅ እፎይታ ነው” ሲሉ ለሁለት ዓመት ያህል የዘለቀው ክርክር መቋጫ ማግኘቱን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X