በዳካር ታሪካዊ ማዕከል የሚገኙ ጎዳናዎች የሴኔጋልን ማንነት የተላበሱ ስያሜ ተሰጣቸው
15:46 06.10.2025 (የተሻሻለ: 15:54 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዳካር ታሪካዊ ማዕከል የሚገኙ ጎዳናዎች የሴኔጋልን ማንነት የተላበሱ ስያሜ ተሰጣቸው
የዋና ከተማዋ አስተዳደራዊና ታሪካዊ ማዕከል የሆነው የዳካር-ፕላቱ ማዘጋጃ ምክር ቤት የቅኝ ግዛት የስያሜ ስምምነቶችን በመሻር፤ በሀገሪቱ ሐይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ህይወት ላይ አሻራቸውን ላሳረፉ ታዋቂ የሴኔጋል ግለሰቦች ክብር ለመስጠት ውሳኔውን ማሳለፉን አስታውቋል።
የስም ለውጥ የተደረገባቸው፦
◻ ሩ ጁልስ ፌሪ ሲባል የነበረው የሙሪድስን ጠቃላይ ኸሊፋ ለማክበር ሩ ሴሪኝ ሙንታካ ምባኬ ሆኗል።
◻ ሩ ፌሊክስ ፎር ሲባል የነበረው የቲዲያንስን ጠቃላይ ኸሊፋ ለማሰብ ሩ ሴሪኝ ባባካር ማንሱር ሲ ተብሏል፡፡
ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦችም እውቅና ተችሯቸዋል፦
◻ የቀድሞው ሩ ፈርዲናንድ ፎች ጎዳና በመጀመሪያው የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል ዣን አልፍሬድ ዲያሎ ተተክቷል፡፡
◻ የቀድሞው ሩ አልበርት ካልሜት ጎዳና በሀገሪቱ የሶሻል ፓርቲ የመጀመሪያው ዋና ፀኃፊ ኡስማን ታኖር ዲየንግ ስም ተሰይሟል፡፡
◻ የቀድሞው ሩ ሳዲ ካርኖት ጎዳና በዳካር የመጀመሪያ መስጊድ አቅኚ ኢማም ማታር ሲላ ተተክቷል፡፡
ሊበሬሽን ጎዳና አሁን ላይ ለቀድሞው ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋድ ክብር በእርሳቸው ስያሜ የሚጠራ ሲሆን ዣን ዣውሬ ጎዳና ደግሞ ወደ ቲዬርኖ ሰይዱ ኑሩ ታል ጎዳና ተለውጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X