ዚምባብዌ ሪከርድ የሆነ ስድስት መቶ ሺ ቶን የስንዴ ምርት ልትሰበስብ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዚምባብዌ ሪከርድ የሆነ ስድስት መቶ ሺ ቶን የስንዴ ምርት ልትሰበስብ ነው
ዚምባብዌ ሪከርድ የሆነ ስድስት መቶ ሺ ቶን የስንዴ ምርት ልትሰበስብ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.10.2025
ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ ሪከርድ የሆነ ስድስት መቶ ሺ ቶን የስንዴ ምርት ልትሰበስብ ነው

የሀገሪቱ የግብርና እና ገጠር ልማት ባለሥልጣን በተሻለ ምርታማነት እና ጠንካራ የመንግሥትና የግል አጋርነቶች በዓመቱ የተቀመጠው ሶስት መቶ ሺ ቶን የስንዴ ምርት የማግኘት ግብ በእጥፍ እንደሚሳካ ይጠበቃል ሲል አስታውቋል።

ከዚምባብዌ ዓመታዊ የ360 ሺ ቶን ፍጆታ በላይ እንደሚሆን የሚጠበቀው ይህ ከፍተኛ ምርት፤ ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች የማያቋርጥ አቅርቦትን ለማረጋገጥና ከውጭ የሚገቡ ውድ ምርቶች ተፅዕኖን ያስወግዳል ተብሏል።

የግብርናና ገጠር ልማት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቲኖ ምሂኮ፤ ምርት የመሰብሰቡ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነና የመጀመሪያው ዙር በአንድ ሄክታር በአማካይ 6.6 ቶን መድረሱን ተናግረዋል። ውጤታማነቱ የአፈር ጤናን እና የውሃ ጥበቃን ትኩረት ባደረጉ ቴክኖሎጂዎች እና ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆኑ የእርሻ ዘዴዎች እንደመጣ አውስተዋል፡፡

የ2025 የስንዴ ምርት ዘመን በተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የዚምባብዌ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ስርጭት ኩባንያ ለመስኖ ሥራ 150 ሜጋ ዋት ተደራሽ ማድረግ ችሏል።

የእህል ግብይት ቦርድ የአምራቾችን ዋጋ በቶን 450 ዶላር ላይ እንዲቆይ ያሳለፈው ውሳኔ በአርሶ አደሮች ዘንድ በተወዳዳሪነቱ እና ዘላቂነቱ ተቀባይነት ማግኘቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መንግሥት አስፈላጊ ግብዓቶችን በወቅቱ ማቅረብ መቻሉ ለታየው አዎንታዊ ምላሽ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተጠቁሟል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0