አልጄሪያ በ2026 በብረት ማዕድን ዘርፍ ራሷን ለመቻል እቅድ አስቀመጠች
11:00 06.10.2025 (የተሻሻለ: 11:04 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አልጄሪያ በ2026 በብረት ማዕድን ዘርፍ ራሷን ለመቻል እቅድ አስቀመጠች
ሁለት የማቀነባበሪያ ዩኒቶች በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ ሲል መንግሥታዊው ሶናሬም ግሩፕ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
የመጀመሪያው ክፍል በ ’ጋራ ጅቤሌት’ ማዕድን ማውጫ ሥፍራ ጋር በሚያዝያ 2026 ሥራ ይጀምራል ተብሏል፡፡ በበሻር የሚገኘውና ከቶስያሊ እና ሲኖስቲል ጋር በመተባበር የተገነባው ሁለተኛው ክፍል በዓመቱ ሁለተኛ አጋማሽ በዓመት ሁለት ሚሊዮን ቶን የብረት ማዕድን ክምችት ያመርታል።
ከቀናት በፊት ይፋ የተደረገው ይህ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት፤ የአልጄሪያን የብረት ማዕድን ኢምፖርት ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው። መሠረተ ልማቶቹ የሀገር ውስጥ አቅርቦቶችን በማጠናከር፣ የአልጄሪያን የብረት ፋብሪካዎችን በመደገፍ፣ ዓለም አቀፍ የገበያ መዋዠቅ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ይቀንሳሉ ሲሉ መገናኛ ብዙኃኑ ዘግበዋል።
የጋራ ጅቤሌት ማዕድን ማውጫ እና አዲሶቹ ዩኒቶች ከሚያዝያ 2026 ጀምሮ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ ዘላቂ የወጪ ንግድ ዕድልም ይኖራቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X