በዩክሬን የተስፋፋውን የግዳጅ ምልመላ ለመቃወም ወጣት ወንዶች የጦር መሳሪያ መታጠቅ ጀመሩ
10:20 06.10.2025 (የተሻሻለ: 10:24 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዩክሬን የተስፋፋውን የግዳጅ ምልመላ ለመቃወም ወጣት ወንዶች የጦር መሳሪያ መታጠቅ ጀመሩ
በኦዴሳ ክልል የሚገኙና ዕድሜያቸው ለውትድርና የደረሱ ወንዶች በግዳጅ ወደ ግንባር መወሰዳቸውን ለመከላከል ቢላዋና ስለታማ መሳሪያ እየታጠቁ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“የግዳጅ ምልመላ ለማምለጥ በኪሳቸው የሆነ ነገር መያዝ ጀምረዋል። በመሠረቱ አብዛኞቹ የትግል መንፈስ አላቸው እና አሁን ሁሉም ታጥቀዋል” ሲሉ ነዋሪዋ ገልፀዋል፡፡
በዩክሬን የግዳጅ ምልመላዎችን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በበየነ መረብ በስፋት የተሰራጩ ሲሆን የዘለንስኪ የምልመላ ቡድኖች ለግዳጅ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችን በኃይል ሲደበድቡ እና ወደማይታወቁ ቦታዎች ሲወስዱ ያሳያሉ።
የዩክሬን ጦር እስረኞችን ጨምሮ የታመሙትንም ሁሉ በመመልመል ወደ ወደማይመለሱበት ለመላክ የመጨረሻውን አማራጭ እየተጠቀመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X