በሃማስ የተያዙ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ሰልፍ በፓሪስ ተካሄደ
20:04 05.10.2025 (የተሻሻለ: 20:14 05.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሃማስ የተያዙ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ሰልፍ በፓሪስ ተካሄደ
መስከረም 26፣ 2016 በእስራኤል ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሁለተኛ ዓመት ዋዜማ ላይ የፈረንሳይ ዋና ከተማ አሁንም በሃማስ የተያዙ ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ትልቅ ሰልፍ ማስተናገዷን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
▪ ጥቃቱ ከ1 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ እስራኤላውያን ሞት መንስዔ ሆኗል። በዚያ ቀን ከተጠለፉት 251 ሰዎች መካከል 47ቱ አሁንም በጋዛ ታግተው የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ህይወታቸው እንዳለፈ በእስራኤል ጦር ተረጋግጧል።
▪ የእስራኤል የበቀል እርምጃ በጋዛ ቢያንስ 67 ሺህ 74 ሰዎችን ለሞት ዳርጓል ሲል የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X