ሩሲያ እና ቬኔዙዌላ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በካሪቢያን የፈፀመውን ጥቃት አወገዙ
18:54 05.10.2025 (የተሻሻለ: 19:04 05.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ቬኔዙዌላ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በካሪቢያን የፈፀመውን ጥቃት አወገዙ
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የቬንዙዌላ አቻቸው ይቫን ጊል ባደረጉት የስልክ ልውውጥ፤ አሜሪካ በካሪቢያን ባሕር በምትወስዳቸው እርምጃዎች ዙሪያ ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው መግለፃቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ላቭሮቭ ሞስኮ በቬኔዙዌላ አቅራቢያ በሚገኙ ዓለም አቀፍ የውሃ አካላት በአንድ መርከብ ላይ አርብ የተፈጸመውን የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት በብርቱ እንደምታወግዝ በውይይቱ ወቅት አጽንዖት ሰጥተዋል።
አሜሪካ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ ያወጀችውን ጦርነት ከሄይቲ አሁናዊ ሁኔታ ጋር በምንም መልኩ እንደማታገናኝ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ማንሳታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X