ናኖ ፓርቲክሎችን ለአዳዲስ የፋሻ ዓይነቶች፣ ፀረ-ባክቴሪያ ሽፋኖች፣ የውሃ ማጣሪያዎች ያዋለችው ወጣት ሩሲያዊ ሳይንቲስት
18:14 05.10.2025 (የተሻሻለ: 18:24 05.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናኖ ፓርቲክሎችን ለአዳዲስ የፋሻ ዓይነቶች፣ ፀረ-ባክቴሪያ ሽፋኖች፣ የውሃ ማጣሪያዎች ያዋለችው ወጣት ሩሲያዊ ሳይንቲስት
ብዙውን ጊዜ "ናኖ ፓርቲክሎች" ጎጂ እንደሆኑ ብናሰብም ከስፑትኒክ ጋር ቆይታ ያደረገችው ሩሲያዊቷ ተመራማሪ ክርስቲና ኮቲያኮቫ ለአስደናቂ ፈጠራዎች ተጠቅማባቸዋለች።
በታዋቂው የሞስኮ MISIS የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲት ሳይንቲስት የሆነችው ክርስቲና፤ ለኮፐር ኦክሳይድ እና ለዚንክ ኦክሳይድ ንጥረ ነገሮች ምስጋና ይግባና ቶሎ የማያገግሙ የቁስል ኢንፌክሽኖችን የሚከላከል እና ፈውስ የሚያፋጥን ፋሻ መሥራት ችላለች።
"በተለያዩ የፈውስ ደረጃዎች እንደሚለዋወጠው የቁስሉ አሲዳማነት፤ ፋሻው ለዚያ የተለየ ደረጃ የሚያስፈልገውን ፀረ-ባክቴሪያ ንጥረ ነገር የሚለቅበትን የፒኤች-ጥገኛ ስርዓት ለመፍጠር አቅደናል" ስትል የሶስት ፈጠራዎች ባለቤቷ እና 27 ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በጋራ ያሳተመችው ተመራማሪዋ አስረድታለች።
ፋሻዎቹ በጥንቸሎች ላይ ተሞክረው "አስደናቂ ውጤት" አስገኝተዋል ስትልም ተናግራለች።
ጠንካራ የፀረ-ባክቴሪያ ሽፋኖች እና አንቲባዮቲኮችን የሚያስወግዱ የግል የውሃ ማጣሪያዎች ሌሎች ፈጠራዎቿ ናቸው።
"የንግድ ሽርክና በመፍጠር እና ያዳበርናቸውን ቴክኖሎጂዎች በመተግበር በመጨረሻ ለህብረተሰቡ እውነተኛ ጥቅሞችን እንዲያመጡ እፈልጋለሁ" ስትል ተመራማሪዋ ሀሳቧን አጠቃላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

