የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ የሀገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ማሻሻያዎች በመከላከል የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ምክረ ሃሳቦችን ውድቅ አደረገ
16:24 05.10.2025 (የተሻሻለ: 16:34 05.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ የሀገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ማሻሻያዎች በመከላከል የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ምክረ ሃሳቦችን ውድቅ አደረገ
የዚምባብዌ የተቀማጭ ባንክ (አርቢዜድ) የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ እና አዲሱ የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዚግ ምንዛሪ እየተረጋጋ መሆኑን በማንሳት፤ አስተዳደሩን በተመለከተ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በቀረበለት ሀሳብ እንደማይስማማ አስታውቋል።
የአርቢዜድ አቋም የሚከተለው ነው፦
🟠 ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን ይከተላል፤ ይህም እየሠራ ነው፡፡
🟠 በ30 በመቶ ሕግ ላይ ጸንቷል፤ ላኪዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን 30 በመቶ ለማዕከላዊ ባንክ መሸጥ አለባቸው፡፡
🟠 ከአይኤምኤፍ የቀረበውን የምንዛሪ ተመንን ሙሉ በሙሉ ነጻ የማድረግ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፤ የባንኩ ይፋዊ የምንዛሪ ተመን በገበያ ላይ እንደተመሠረተ ገልጿል፡፡
🟠 ትክክለኛ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ገበያ ከተገነባ በኋላ ብቻ ለቀጣይ ማሻሻያዎች ዝግጁ ይሆናል፡፡
🟠 በ2030 ወጥ የምንዛሪ መገበያያ እርሱም ዚግ ብቻ ይሆናል የሚል ግብ አስቀምጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X