የህዳሴ ግድብን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አዳዲስ የአገልግሎት ጥቅሎች ይፋ ሊደረጉ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየህዳሴ ግድብን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አዳዲስ የአገልግሎት ጥቅሎች ይፋ ሊደረጉ ነው
የህዳሴ ግድብን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አዳዲስ የአገልግሎት ጥቅሎች ይፋ ሊደረጉ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.10.2025
ሰብስክራይብ

የህዳሴ ግድብን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አዳዲስ የአገልግሎት ጥቅሎች ይፋ ሊደረጉ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በአዳዲስ የጉብኝት ጥቅሎችና ትብብሮች ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

"የግድቡ የገዘፈ ታሪክ ብቻውን ጎብኝዎችን የመሳብ አቅም አለው። በግድቡ ሥፍራ የተፈጠረው ሐይቅ ከአራት እስከ አምስት የሚደርሱ ልዩ ልዩ የቱሪዝም አገልግሎት ጥቅሎችን ለማዘጋጀት እድል ይሰጣል" ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ  እንደገና አበበ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ ተናግረዋል።

ቦታውን ልዩ እና ማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የማስተዋወቅ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የትብብር ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል።

የማስተዋወቅ እና የጉብኝት ጥሪ ዘመቻዎች በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቁ በኋላ ጥቅሎቹ ይፋ እንደሚሆኑም አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0