ጢያ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስን ለማልማት ያለመ የ3.5 ቢሊዮን ብር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጀመረ
12:25 05.10.2025 (የተሻሻለ: 12:34 05.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጢያ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስን ለማልማት ያለመ የ3.5 ቢሊዮን ብር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጀመረ
በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ የሚገኘውን የጢያ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስና አካባቢውን በማልማት ተመራጭ የመስህብ ስፍራ ለማድረግ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘውና በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የጢያ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ በማልማትና የገቢ ምንጭ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ወጪው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ፣ ከባለሀብቱና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል።
የግንባታ ሥራው የሚያካትታቸው፦
ሆቴል፣
የመዝናኛ ስፍራዎች፣
የግብይት ማዕከላት፣
የመሰብሰቢያ አዳራሾች።
የጢያ መካነ ቅርስ በተለያየ ርቀት ላይ የተቀመጡ ቁጥራቸው ከ41 እስከ 48 የሚደርስ ትክል ድንጋዬች መገኛ ሲሆን በ1972 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና እና ባሕል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም አቀፍ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ እነዚህ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ባሕል ቅሪቶች ከ12ኛው እስከ 14ኛው ክፍለ ዘመን እንደቆሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X