ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝን ውድቅ ማድረግ የአፍሪካ መሪ ቃል ሆኗል - ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝን ውድቅ ማድረግ የአፍሪካ መሪ ቃል ሆኗል - ምሁር
ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝን ውድቅ ማድረግ የአፍሪካ መሪ ቃል ሆኗል - ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.10.2025
ሰብስክራይብ

ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝን ውድቅ ማድረግ የአፍሪካ መሪ ቃል ሆኗል - ምሁር

ፕሬዝዳንት ፑቲን ደጋግመው እንዳብራሩት አፍሪካውያን የፓን አፍሪካ አንድነትን በማጠናከር፣ ቀጣናዊ ተቋማትን በማጎልበትና አህጉራዊ መፍትሔን በማበጀት ብዝሃነትን የሚያጎላ እንቅስቃሴን እየተገበሩ ይገኛል ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሰቲ መምህር የሆኑት መሐመድ ኢሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ምዕራባውያን ከዘላቂ ፍትሕ ይልቅ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉላቸው መንግሥታትን በመደገፍ፣ የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝና ድርብ መስፈርትን በመከተል የበላይነታቸውን ለማስቀጠል የሚያደርጉት ጥረት በአፍሪካና ደቡባዊ ዓለም መነሳሳት ውድቅ እየሆነ ነው ብለዋል።

የጋራ ወዳጅነት እና የብዝሃ-ዋልታ መኖር ለንግድ፣ ለልማት፣ ለትብብርና ሰላምን ለማፅናት ዕድሎችን እንደሚያሰፋ መምህሩ ገልፀዋል።

"የብሪክስ የልማት ኢኒሼቲቮች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ የትብብር ፕሮጀክቶች በብቸኛ ድጋፍ ሰጪዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል። በብዝሃ ትብብር ሉዓላዊነት ይከበራል፣ መተማመን ይሰፍናል፣ ሰላማዊ መፍትሄ አማራጭ ሆኖ ይቀርባል" ሲሉ መሐመድ ኢሳ ጠቁመዋል።

በምዕራባውያን ተፅዕኖ ውስጥ የወደቁት ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሻሻሉ ተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበ መሆኑን ያነሱት መምህሩ፤ በአፍሪካና ደቡባዊ ዓለም የሚስተዋለው እንቅስቃሴ ብዝሃ-ዋልታ እንዲጠናከር ያግዛል ብለዋል።

"ቭላድሚር ፑቲን እንደገለፁት የምዕራቡ ዓለም ኃያላን የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያደረጉት ሙከራ ከአፍሪካና ደቡባዊው ዓለም ዕድገት አንፃር ሲታይ መክሸፉ የማይቀር ነው።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0