በትራምፕ ዕቅድ ላይ የተመሰረተው የጋዛ ድርድር እሁድ በግብፅ ይጀምራል
16:43 04.10.2025 (የተሻሻለ: 16:44 04.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በትራምፕ ዕቅድ ላይ የተመሰረተው የጋዛ ድርድር እሁድ በግብፅ ይጀምራል
የትራምፕ ልዩ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ ወደ ግብፅ ጉዞ መጀመራቸውን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
የእስራኤል ልዑካን ቡድን በስትራቴጂክ እቅድ ሚኒስትር እና የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ታማኝ ረዳት በሆኑት በሮን ደርመር ሊመራ እንደሚችል ተዘግቧል።
ቴል አቪቭ እስራኤላውያን ታጋቾችን ማስፈታት እና የፍልስጤም እስረኞችን መለቀቅ የሚያካትተውን የትራምፕ የጋዛ የሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራዊ ለማድረግ፤ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እየተዘጋጀች ነው ሲል የእስራኤል መንግሥት ምንጭ ቅዳሜ ማለዳውን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X