የሩሲያ የኒውክሌር ኩባንያ ሮሳቶም በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሕክምና አገልግሎት ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችል ውይይት አካሄደ
15:30 04.10.2025 (የተሻሻለ: 15:34 04.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የኒውክሌር ኩባንያ ሮሳቶም በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሕክምና አገልግሎት ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችል ውይይት አካሄደ
የኩባንያው የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ አገልግሎቱን ለማስፋትና ውጤታማ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል መሠረት ጥሏል፡፡
በውይይቱ የተነሱ ነጥቦች፦
ለኒውክሌር ሕክምና አገልግሎቶች አስፈላጊ ግብዓት ማቅረብ፣
የመሠረተ ልማት ግንባታ እና በሰው ኃይል ልማት፣
በምርምር ዘርፍ ትብብር ማጠናከር።
የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እውን ለማድረግ የወጠነው ሀገራዊ ፕሮጀክት የኒውክሌር ኃይልን ለብሔራዊ ልማት እና ለላቀ የጤና አገልግሎት በሰላማዊ መንገድ መጠቀምን ከሚደግፉ ብሔራዊ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፖሊሲዎች ጋር ፍጹም የተጣጣመ ነው ሲል ኮሌጁ ጠቁሟል።
"ተቋማችን እና ሀገራችን ለዚህ ውስብስብ የቴክኖሎጂ መስክ አዲስ በመሆናቸው፣ እነዚህን ወሳኝ አገልግሎቶች በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ እና ለማቅረብ የሮሳቶም ቴክኒካዊ መመሪያ ወሳኝ ነው" ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X