ለሱዳን ጎርፍ ኢትዮጵያን ተጠያቂ ያደረገው የግብፅ ሀሰተኛ ውንጀላ መሠረተ ቢስ ነው - ኢትዮጵያ
13:48 04.10.2025 (የተሻሻለ: 13:54 04.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለሱዳን ጎርፍ ኢትዮጵያን ተጠያቂ ያደረገው የግብፅ ሀሰተኛ ውንጀላ መሠረተ ቢስ ነው - ኢትዮጵያ
የግብፅ የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስቴር ውንጀላ መሠረተ ቢስ ነው ያለው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ፤ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ በፊት ያሉና አሁናዊ መረጃዎችን በማስረጃነት አቅርቧል።
ከህዳሴ ግድበ ግንባታ በፊት የነበረው የጎርፍ መጠን
በነሐሴ ወራት በቀን ከ800 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ፣
በመስከረም ወራት በቀን ከ750 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ይደርስ ነበር።
ከግድቡ ግንባታ በኋላ የጎርፍ መጠኑ
በነሐሴ 2025 ዕለታዊ የውሃ መጠን 154.7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ፣
በመስከረም 2025 472 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ነበር።
"የሕዳሴ ግድብ በላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ከፍተኛ የዝናብ ወቅት የተለመደ የነበረውን አውዳሚ ጎርፍ በመቆጣጠር የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ማሕበረሰቦችን ህይወት እና ንብረት ይጠብቃል። ሕዳሴ ግድብ ባይኖር ኖሮ ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የተስተዋለው ከባድ ዝናብ በሱዳንና በግብፅ የሰው ሕይወትና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ታሪካዊ ውድመት ሊያስከትል ይችል ነበር፡፡"
የሱዳን የግብርና እና መስኖ ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተከሰተው ጎርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ማንሳቱን የጠቀሰው መግለጫው፤ ግብጽ በተቃርኖ በመቆም ዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ ለማሳሳት ሀሰተኛ ክስ አቅርባለች ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሱዳን ጋር የመረጃ ልውውጥ እና ትብብር ማዕቀፍን በማቋቋም አውዳሚ የጎርፍ መጠንን በመቀነስ ግድቡ ለሱዳን በረከት ሆኖ እንዲቀጥል ከሚመለከታቸው የሱዳን ባለሥልጣናትና ባለሙያዎች ጋር በቅርበት መሥራቷን እንደምትቀጥል አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X