የባሕር በር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የኅልውና ጉዳይ መሆኑን አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የባሕር በር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የኅልውና ጉዳይ መሆኑን አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ ተናገሩ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አገሪቱ አብሮ በማልማት፣ በሊዝ (ኪራይ) አሊያም ይዞታ በመለዋወጥ የወደብ ተጠቃሚ ለመሆን ላቀረበችው ጥያቄ ከጎረቤቶቿ ቀና ምላሽ እንደምትጠብቅም ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"በታሪካዊ ስህተት ያስነጠቅነው የባሕር በር ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል። ይህን ስህተት ለማረም ከጎረቤቶቻችን ጋር ተቀራርቦ መነጋገር እና መደራደር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ሰላም የከፈለችውን መስዕዋትነትም መዘንጋት አይገባም።" ብለዋል።

አምባሳደሩ የባሕር በር ቀጣናዊ ስጋቶችን ለመከላከል ያለውን እገዛም አውስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0