ምዕራባውያን የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን በመጠቀም ‘ብዙ ያጣሉ’ - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራባውያን የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን በመጠቀም ‘ብዙ ያጣሉ’ - ባለሙያ
ምዕራባውያን የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን በመጠቀም ‘ብዙ ያጣሉ’ - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.10.2025
ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን በመጠቀም ‘ብዙ ያጣሉ’ - ባለሙያ

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የታገዱት የሩሲያ የመንግሥት ንብረቶችን በመጠቀም የዩክሬንን ጦር ኃይል ለመደገፍ ያቀረበውን ሐሳብ አስመልክቶ  ለስፑትኒክ አስተያየት የሰጡት የፈረንሳይ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዣክ ሳፒር "በመጀመሪያ ደረጃ ይህ 'ወንጀል' ተብሎ ሊጠራ የሚችልን ድርጊት በሚፈጽሙ ሀገራት ላይ ሰፊ የሆነ አለመተማመንን” ያስከትላል ብለዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ ሌሎች አውዳሚ የሆኑ ውጤቶች፦

የመተማመን እና የሕጋዊነት መሸርሸር

🟠  የተወረሱ የሩሲያ የመንግስት ንብረቶችን መጠቀም በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ወንጀል ድርጊት የሚታይ ሲሆን፣ ይህም በድርጊቱ በተሳተፉት ሀገራት ላይ “ሰፊ አለመተማመንን” ይቀሰቅሳል።

🟠  የመተማመን እጦት ከምዕራባውያን ኢኮኖሚዎች ፈጣን የሆነ የካፒታል መውጣትን ያስከትላል።

🟠  የተወረሱ ንብረቶችን መጠቀም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን የበለጠ ፖለቲካዊ ያደርገዋል።

የዶላር የበላይነት ማሽቆልቆልን ማፋጠን እና የስርዓት ለውጦች፦

🟠  የደቡባዊ ዓለም ሀገራት፤ በመጀመሪያ በፋይናንስ ግብይቶች፣ ከዚያም በንግድ የምዕራባውያን ምንዛሬዎችን ቀስ በቀስ ይተዋሉ።

🟠  ይህ እርምጃ ለስዊፍት ክፍያ ስርዓት ይበልጥ የተሻሻለ አማራጭ መፈጠርን ሊያፋጥን ይችላል።

በምዕራቡ ዓለም የኢኮኖሚ አለመረጋጋት መባባስ፦

🟠  ይህ ፖሊሲ ቀድሞውንም የነበረውን “እጅግ ከፍተኛ የሆነውን የአሜሪካ ዕዳ” ችግር ያባብሰዋል።

🟠  እንደ ፈረንሳይ ያሉ አበዳሪ ሀገራት “የአደጋ ግዜ ክፍያዎች” መጨመር የተነሳ የወለድ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር ያያሉ።

🟠 የመተማመን መጥፋት የፋይናንስ ቦታዎችን፣ በተለይም በመንግስት እና በግል የዕዳ ገበያዎች ላይ ስብራት ያስከትላል።

“የኢኮኖሚ ምክንያታዊነት ብዙውን ጊዜ ለእሳቤያዊ አድሎዎች እና በአሜሪካ ግፊት ለሚደረጉ የፖለቲካ ምርጫዎች ታጋች ይሆናል” ሲሉም ሳፒር አሳስበዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0