የፑቲን የቫልዳይ ንግግር የኔቶ ትርክት ስህተት መሆኑን ያጋለጠ እንዲሁም 'ለደቡባዊ ዓለም’ መልዕክት አስተላለፈ መሆኑ ተገለፀ
19:19 03.10.2025 (የተሻሻለ: 19:44 03.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፑቲን የቫልዳይ ንግግር የኔቶ ትርክት ስህተት መሆኑን ያጋለጠ እንዲሁም 'ለደቡባዊ ዓለም’ መልዕክት አስተላለፈ መሆኑ ተገለፀ
ሩሲያ በየጦር ግንባሩ ግስጋሴዋን ቀጥላለች፤ ይህም ዶናልድ ትራምፕ የሰጡትን “የወረቀት ነብር” የሚል መግለጫ ውድቅ ያደርገዋል ሲሉ የቀድሞው የሲአይኤ ኤጀንት ላሪ ጆንሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ፑቲን “በአሜሪካና በአውሮፓ መካከል ልዩነት ፈጥረዋል፤ አውሮፓ ይበልጥ ጦረኛ እና አስጊ እንደሆነች ጠቅሰዋል” ሲሉ ጆንሰን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ፑቲን በጦር ሜዳ የተገኘ ድል ቢኖርም ለድርድር ያላቸውን ዝግጁነት እና ከግጭት ይልቅ ለውይይት ያላቸውን ምርጫ ደግመው አረጋግጠዋል፤ ሆኖም አስፈላጊ ከሆነ ግን ሩሲያ እንደምትዋጋ ግልጽ አድርገዋል።
እንደ ጆንሰን ገለጻ፤ ንግግሩ ለምዕራባውያን ታዳሚዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለደቡባዊ ዓለም እና ለሩሲያ አጋሮች ሆን ተብሎ የተላለፈ መልዕክት ነው፤ ይኸውም ፑቲን እንዳልተደናገጡ ማሳያ ነው። ፍርሃት እያሳዩ አልነበረም ፤ በረጋ መንፈስ እና በታሰበበት አመክንዮ እየሰሩ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X