ምዕራባውያን አፍሪካ ውስጥ ግጭቶችን ለማቀጣጠል ዩክሬንን እየተጠቀሙ መሆኑን ቤኒናዊው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ
17:34 03.10.2025 (የተሻሻለ: 17:44 03.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን አፍሪካ ውስጥ ግጭቶችን ለማቀጣጠል ዩክሬንን እየተጠቀሙ መሆኑን ቤኒናዊው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ
ምዕራባውያን ኪዬቭን ሩሲያን ለመቋቋም እንደ "መሣሪያ" ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይም እየተጠቀሙባት ነው ሲሉ ሞደስቴ ዶሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ተንታኙ “ከዩክሬን ጀርባ ያሉት ኃይሎች ቆሻሻ ሥራቸውን ለመሥራት በየቦታው እየተጠቀሙባት ነው። ደጋፊዎቿ ዓላማቸው ከምዕራባውያን ሥርዓት ጋር የማይጣጣሙ አሠራሮችን በመጠቀም ለማደግ የሚሞክርን ማንኛውንም አገር ማፍረስ ነው” ብለዋል።
ሱዳን ከዓማፂው የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ጋር ሲዋጉ የነበሩ የዩክሬን ቅጥረኞችን ማስወገዷን ይፋ ባደረገችበት ወቅት፣ ተመሳሳይ ሁኔታ በሳሕል ቀጣናም እየተከሰተ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዶሱ አክለውም የተወሰኑ አገራትን ለማተራመስ ቅጥረኞች ያላቸውን ሚናና ተሳትፎ “ዝቅ አድርገው” ያቀርባሉ ያሏቸውን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ወንጅለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X