ሱዳን የታላቁ የሕዳሴ ግድብን የመገምገም እቅድ እንዳላት አስታወቀች
17:09 03.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 03.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን የታላቁ የሕዳሴ ግድብን የመገምገም እቅድ እንዳላት አስታወቀች
ከተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መልስ ፖርት ሱዳን ውስጥ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ፤ አገራቸው ግምገማውን ማካሄድ የመትፈልገው ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንደ ሱዳን ሚዲያ ዘገባ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ “ዝርዝር ግምገማዎችን” ማድረግ ያስፈለገው “ወደፊት የሚመጡ አደጋዎችን ለማስወገድ” ነው፡፡
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በጥቁር ዓባይ እና በነጭ ዓባይ የውሃ መጠን መጨመር ዙሪያ ተወቃቅሰዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X