ጋና የተባረሩ ሰዎች ‘መጣያ’ አትሆንም ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ
14:59 03.10.2025 (የተሻሻለ: 15:04 03.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጋና የተባረሩ ሰዎች ‘መጣያ’ አትሆንም ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ አምባሳደሮችና ከፍተኛ ኮሚሽነሮችን ሲሾሙ፣ የጋና ሉዓላዊነትና ደህንነት ዋና ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከአሜሪካ ተባርረው የሚመጡ አፍሪካውያንን ለመቀበል የተደረገው ስምምነት “ውስን፣ በጥንቃቄ የተጣራ እና የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) ፕሮቶኮሎቻችን ጋር የተጣጣመ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ የጋና የውጭ ጉዳይ ተልዕኮዎች ከስሜታዊነት የራቀና ይበልጥ ንቁ የሆነ አቋም እንዲወስዱ አሳስበዋል።
ማሃማ “ንቁ ተሳታፊ በመሆን እድሎችን መፈለግ፣ ፍትሐዊ ስምምነቶችን መደራደር እና የጋና ጥቅም ፈጽሞ እንዳይጎዳ ማረጋገጥ አለባቸው” ብለዋል።
አሜሪካ “ወደ ሦስተኛ አገር የማባረር” ፖሊሲ ለመተባበር እምቢተኛ የሆኑ አገራት ላይ የቪዛ ገደቦችን በመጣል ወንጀለኞች ጨምሮ የተባረሩ (ዲፖርት የተድረጉ) የውጭ ዜጎችን እንዲቀበሉ የአፍሪካ አገራትን እየተጫነች ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X