የቡድን 7 በ2025 በእገዳ ላይ ከሚገኘው የሩሲያ ሀብት 26.5 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ፈንድ ማድረጉን የስፑትኒክ ትንተና አረጋገጠ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቡድን 7 በ2025 በእገዳ ላይ ከሚገኘው የሩሲያ ሀብት 26
የቡድን 7 በ2025 በእገዳ ላይ ከሚገኘው የሩሲያ ሀብት 26 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.10.2025
ሰብስክራይብ

የቡድን 7 በ2025 በእገዳ ላይ ከሚገኘው የሩሲያ ሀብት 26.5 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ፈንድ ማድረጉን የስፑትኒክ ትንተና አረጋገጠ

ስፑትኒክ በዩክሬን ፋይናንስ ሚኒስቴር እና በአውሮፓ ኮሚሽን መረጃ ላይ ባደረገው ስሌት መሠረት፣ ለኪዬቭ በብድር ከተሰጠው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን በዚህ ዓመት የዩክሬን የውጭ በጀት ፋይናንስ ውስጥ ሦስት አራተኛውን ይይዛል።

ቁልፍ አኃዞች፡

▪ በጠቅላላ በቡድን ሰባት ያፀደቀው ብድር፡ በግምት 50 ቢሊዮን ዶላር (ከታገደው የሩሲያ ሀብት በሚገኝ ገቢ የሚሸፈን)፤ ከመስከረም ጀምሮ 26.5 ቢሊዮን ዶላር ቀደም ብሎ ተመድቧል።

▪ የገንዘብ ዝውውር ክፍፍል:

• የአውሮፓ ሕብረት፤ 15.8 ቢሊዮን ዶላር

• ካናዳ፤ 3.4 ቢሊዮን ዶላር 

• ጃፓን፡ 3.3 ቢሊዮን ዶላር

• እንግሊዝ፤ 3 ቢሊዮን ዶላር እና

• አሜሪካ፤ 1 ቢሊዮን ዶላር (የመጀመሪያው ክፍያ፣ እ.አ.አ በ2024 መጨረሻ)።

ከ2022 ጀምሮ የአውሮፓ ሕብረት እና የቡድን 7 ወደ 300 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ የሩሲያ የውጭ ክምችት አግደዋል። ከዚህ ውስጥ 200 ቢሊዮን ዩሮ የሚሆነው በአውሮፓ ውስጥ፣ በአብዛኛው በቤልጂየም በሚገኘውና በዓለማችን ትልቁ የካቢታል ገበያ ተቋማት አንዱ በሆነው በዩሮክሊር ተይዟል።

ሞስኮ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገንዘብ መታገዱን በተደጋጋሚ "ስርቆት" በማለት አውግዛለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ላቭሮቭ ሞስኮ በሩሲያ ውስጥ የተያዙ የምዕራባውያን ንብረቶችን በመውረስ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0