ከአቡጃ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የፓን-አፍሪካ የቱሪዝም ልዑካን ቡድን ጉዞ ተጀመረ
13:25 03.10.2025 (የተሻሻለ: 13:34 03.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከአቡጃ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የፓን-አፍሪካ የቱሪዝም ልዑካን ቡድን ጉዞ ተጀመረ
ይህ አዲስ የቱሪዝም ተነሳሽነት ቀጣናዊ ውህደትን ለማጠናከር እና የጋራ ባሕላዊ ቅርስን ለማክበር ያለመ ሲሆን በትናንትናው ዕለት በናይጄሪያ አቡጃ በይፋ ተጀምሯል።
“ቱሪስም በመላው አፍሪካ ፕሮጀክት” ተብሎ የተሰየመው ይህ ጉዞ "በጄት ኤጅ ኔሽን ቢልደርስ" የተደራጀ ሲሆን፣ ልዑካን ቡድኑ በመንገዳቸው ላይ ሰባት የአፍሪካ አገራትን በየብስ አቋርጦ ከናይጄሪያ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛል።
በመነሻ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኘት በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሠ ገረመው፣ ተነሳሽነቱን “በቱሪዝም እና በባሕል ዲፕሎማሲ የአፍሪካን አንድነት ወደፊት ለማራመድ ወቅታዊ እና ገንቢ እርምጃ” ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ