ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ

የዳንጎቴ ግሩፕ መሥራች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት የማስፋት ፍላጎት እንዳላቸውም በትናንትናው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል፡፡

ዳንጎቴ አክለውም መንግሥት ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎችና የኢኮኖሚው ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መሆን ለኢንቨስትመንት እድገት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

የመዳበሪያ ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ አልፎ የጎረቤት ሀገራትን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ያረጋግጣል ሲሉ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር የገቡበትን አጋርነት አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሥራዎች ሀገሪቱ በአፍሪካ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ መግቢያ በር እንደሚያደርጋት ተናግረዋል ሲሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0