የተዋሐደች አፍሪካን እውን ለማድረግ ጠንካራ አኅጉራዊ ትርክት መትከል ይገባል - የሰላም ግንባታ እና የግጭት አፈታት ባለሙያ
20:43 02.10.2025 (የተሻሻለ: 20:54 02.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የተዋሐደች አፍሪካን እውን ለማድረግ ጠንካራ አኅጉራዊ ትርክት መትከል ይገባል - የሰላም ግንባታ እና የግጭት አፈታት ባለሙያ
አፍሪካ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሐብት ሕዝቧቿን ለማልማት ማዋል እንድትችል፤ ከፋፋይ የቅኝ ግዛት እሳቤዎችን መዋጋት እንዳለባት ገለታ ሴሜሶ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ባለሙያው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሕጉሪቱ በራስ አቅም መልማት የመቻል መንፈስን በትውልዱ ሥነ-ልቦና ውስጥ ማስረጽ እንዳለባትም ገልጸዋል።
"የተባበረች አፍሪካን እውን ለማድረግ ሰላም ወሳኝ ነው። አፍሪካ በተፈጥሮ ሃብት እና በሰው ሃይል ረገድ ሁሉን የታደለች አሕጉረ ናት። 'ዘመናዊ' እና አገር በቀል ዕውቀትን በማስተባበር በአንድነት መስራት አለብን።" ብለዋል።
ገለታ ሴሜሶ (ዶ/ር) አሕጉሪቱ ማፍረስ እና መልሳ መገንባት አለባት ያሏቸውን ጉዳዮችም አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X