ባለብዙ ዋልታነት እና ባለብዙ-ማዕከልነት ለረጅም ጊዜ ከእኛ ጋር የሚኖሩ እውነታዎች ናቸው ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
19:59 02.10.2025 (የተሻሻለ: 20:04 02.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባለብዙ ዋልታነት እና ባለብዙ-ማዕከልነት ለረጅም ጊዜ ከእኛ ጋር የሚኖሩ እውነታዎች ናቸው ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
የፑቲን ስለ ባለብዙ-ዋልታ ዓለም የሰጡት መግለጫ ቁልፍ ሃሳቦች ፦
ባለብዙ-ዋልታ ዓለም የበለጠ ዲሞክራሲያዊ ነው።
በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ ዓለም አቀፍ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚፈልጉ ያህል ብዙ አገሮች ከዚህ በፊት ታይተው አያውቁም።
በዓለም ላይ የሚደረጉ ማንኛውም ውሳኔዎች ለሁሉም ወይም ለአብዛኛው ተስማሚ በሆኑ ስምምነቶች ላይ ብቻ ሊመሰረቱ ይችላሉ፤ ካልሆነ ግን ዘላቂነት የላቸውም።
ባለብዙ-ዋልታነት የመጣው ምዕራባውያን ዓለም አቀፋዊ የበላይነትን ለማስጠበቅ ባደረጉት ሙከራ ምክንያት ነው።
የቀድሞው ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተቋማት ኃይላቸውን አጥተዋል።
የብሪክስ እና የሌሎች ክልላዊ ማህበራት መስፋፋት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዲፕሎማሲ መንፈስ ነው።
በዓለም ላይ እየፈጠሩ ያሉት አዳዲስ ማኅበራት የተፈጠሩት በተዋረድ መርህ አይደለም።
ጥቂት አገሮች የቀረውን ዓለም እንዴት መኖር እንዳለበት ይወስኑ የነበሩበት ዘመን ላይመለስ አልፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X