የሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና ብሪክስ ተፅዕኖ በዓለም ዙሪያ እያደገ ነው - ፑቲን
19:38 02.10.2025 (የተሻሻለ: 10:14 03.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና ብሪክስ ተፅዕኖ በዓለም ዙሪያ እያደገ ነው - ፑቲን
ፑቲን እንዳሉት፣ ብሪክስ መጎልበት የጀመረው ድርጅቱ አንድን አቋም ከማስገደድ ይልቅ የጋራ ጥቅሞችን እንደሚያስቀድም ሁሉም ስለተገነዘቡ ነው።
ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በስምምነት ለመፍታት ካለው ፍላጎት የተነሳ አዳዲስ ተቋማት ተመሠረቱ። ለምሳሌ፣ የሻጋይ ትብብር ድርጅት እና ብሪክስ የተፈጠሩት በዚህ መንገድ ነው።
የብሪክስ አገሮች በጋራ ፍላጎቶች በድርጅቱ ውስጥ የተሰባሰቡ ተፈጥሯዊ አጋሮች ናቸው ብለዋል።
የአውሮፓ የደህነት እና የትብብር ድርጅት በድህረ-ሶቪዬት ሕብረት የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን መወያያ መድረክነት ተቀይሯል። አዎ፣ እንደነዚህ ያሉ ችግሮች ነበሩ፣ ነገር ግን ተመሳሳይ ችግሮች በምዕራቡ ዓለምም ይስተዋሉ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት፣ የአውሮፓ የደህነት እና የትብብር ድርጅት የተቋቋመው ለተለያዩ ዓላማዎች ሲሆን፣ ፖለቲካዊ ባህሪ በማግኘቱ የመጀመሪያ ትርጉሙን አጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X