ሩሲያ ማዕቀቦችን በመቋቋም በጣም ከፍተኛ የጥንካሬ አቅሟን ማሳየቷን ፑቲን ገለፁ
18:53 02.10.2025 (የተሻሻለ: 19:04 02.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ማዕቀቦችን በመቋቋም በጣም ከፍተኛ የጥንካሬ አቅሟን ማሳየቷን ፑቲን ገለፁ
ሩሲያ ለዓለም አስፈላጊ በመሆኗ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ልትገፋ አትችልም ሲሉ ፑቲን ተናገሩ
ሞስኮ በሌለችበት የዓለምን ሚዛን - በስትራቴጂያዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም በባህላዊ ደረጃ ማስጠበቅ አይቻልም ብለዋል።
አሁንም ቢሆን አንዳንዶች በሞስኮ ላይ ስትራቴጂያዊ ሽንፈት ለማድረስ እየሞከሩ ነው፤ ነገር ግን በጣም ግትር የሆኑት ሰዎች እንኳን ይህ የማይቻል መሆኑን በመጨረሻ ይገነዘባሉ ሲሉ አክለዋል።
በሩሲያ ላይ የተጣሉት የቅጣት እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ ሳይሳኩ ቀርተዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሩሲያ ኔቶን ልታጠቃ ትችላለች የሚሉ መግለጫዎች “ከንቱ ናቸው” ናቸው
ለምዕራባውያን ልሂቃን ባስተለልፉት መልዕክት “ተረጋጉ፣ በደንብ ተኙ በመጨረሻም ችግራችሁን ተወጡ” ብለዋቸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X