ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅትን 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቷ በመድኃኒት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል - የጤና ሚንስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅትን 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቷ በመድኃኒት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል - የጤና ሚንስትር
ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅትን 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቷ በመድኃኒት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል - የጤና ሚንስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅትን 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቷ በመድኃኒት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል - የጤና ሚንስትር

ዶክተር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር የተሰጣትን እውቅና አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኘው ውጤት ለኅብረተሰቡ ጥራቱን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመድኃኒት አቅርቦት ከማረጋገጥ ባሻገር፣ በአገሪቱ በመድኃኒት ምርት ለተሠማሩ አካላት ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ኢትትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በብቸኝነት ያስመዘገበችው ውጤት በዘርፉ ባለሃብቶችን ለመሳብ እና በመድኃኒት አቅርቦት፣ ቁጥጥርና እና ቅብብሎሽ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርትን ብሔራዊ መርሃግብርን እንደሚደግፍ እና ለተኪ ምርቶች የተሰጠውን ትኩረት  ለማጠናከር እንደሚያግዝ ዶክተር መቅደስ ጨምረው ገልጸዋል።

ቀጣዩን 4ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0