የኢትዮጵያ የጥጥ ምርት የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
15:10 02.10.2025 (የተሻሻለ: 15:14 02.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የጥጥ ምርት የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የጥጥ ምርት የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ይህ የምርት እድገት የታየው ባለፉት ሦስት ዓመታት የጥጥ ምርታማነትንና ጥራትን የሚያሻሻሉ ሥራዎች በመከናወናቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ጥጥ ማኅበር አስታወቋል።
በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሳምሶን አሰፋ፣ ምርታማነትንና ጥራትን የሚያሻሻሉ ስራዎች በመከናወናቸው ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሀገር ውስጥ ፍጆታን በመሸፈን በአነስተኛ መጠን ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ግብርና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአሁኑ ወቅት 113 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 71 ሺህ ሜትሪክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ ይጠበቃል። በጥጥ እሴት ሰንሰለት ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የጥጥ ልማት የባለድርሻ አካላት ጥምረት እየተቋቋመ መሆኑንም ገልጿል።
እሴት የጨመሩ ምርቶችን ማቅረብ፣ የተሻሻሉ አዳዲስ ዝርያዎችን ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስርና የፋይናንስ ድጋፍን ማጠናከር፣ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎችን ተደራሽነት ማስፋትና ማዘመን ላይ በትኩረት ይሰራል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X