ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የኒውክሌር ልማት ስምምነት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ተስፋ ነው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የኒውክሌር ልማት ስምምነት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ተስፋ ነው - ባለሙያ
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የኒውክሌር ልማት ስምምነት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ተስፋ ነው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የኒውክሌር ልማት ስምምነት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ተስፋ ነው - ባለሙያ

ባለፈው ሳምንት ሞስኮ ውስጥ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሳምንት ዝግጅት ላይ በበየነ መረብ ተሳትፎ ያደረጉት የዲፕሎማሲ ጉዳዩች አንቂው ኑርሁሴን አሊ፣ የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያን የኢነርጂ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ልማት የሚደገፍ መሆኑን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል።

አክለውም አገሪቱ የብሪክስ አባል መሆኗ እሳቸውን ጨምሮ ለብዙ ወጣቶች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ማምጣቱን አስታውቀዋል።

" ... ከአራት ወራት በፊት ሩሲያ ውስጥ በነበረበኝ ቆይታ ከተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ተወካዩች ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር ለተማሪዎቻቸው የእውቀት መጋራት የሚፈጥሩባቸውን ስምምነቶች ተፈራርመዋል" ሲሉ አስታውሰዋል።

ኑርሁሴን የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ ሩሲያ በምታዘጋጃቸው ታላላቅ ዓለም አቀፍ ፎረሞች እና ኮንፈረንሶች ላይ መሳተፋቸው የወጣት ችግሮችን በወጣት እንዲፈቱ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0