እስራኤል ዓለም አቀፍ ሱሙድ ፍሎቲላን መያዟ የሽብር ድርጊት ነው - የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእስራኤል ዓለም አቀፍ ሱሙድ ፍሎቲላን መያዟ የሽብር ድርጊት ነው - የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
እስራኤል ዓለም አቀፍ ሱሙድ ፍሎቲላን መያዟ የሽብር ድርጊት ነው - የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2025
ሰብስክራይብ

እስራኤል ዓለም አቀፍ ሱሙድ ፍሎቲላን መያዟ የሽብር ድርጊት ነው - የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  

"ለጋዛ ህዝብ የሰብአዊ ዕርዳታ ለማድረስ በዓለም አቀፍ ውሀ ላይ በመጓዝ ላይ በነበረው በዓለም አቀፍ ሱሙድ ፍሎቲላ (እርዳታ የጫኑ ጀልባዎች) ላይ በእስራኤል ኃይሎች የተፈፀመው ጥቃት፤ ዓለም አቀፍ ሕግን በእጅጉ የሚጥስ እና የንፁሀን ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል የሽብር ድርጊት ነው" ሲል መግለጫው ያስነብባል።

የቱርክ ፓርላማ አባልና የሱሙድ ፍሎቲላ ተሳታፊ የሆኑት ነጅመቲን ቻሊሽካን ከመንግሥት ባለሥልጣናት ተጨማሪ ምላሽ እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

"አሜሪካ ውስጥ ድርድር ቢኖርም፣ እስራኤል ለፍሎቲላው ምንም ዓይነት መቻቻል ሳታሳይ የመርከቦቹን መንገድ ዘግታለች። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዓለም አቀፍ ተዋናዮች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ ብዬ አስባለሁ... በመጀመሪያ ከፕሬዝዳንታችን ጨምሮ ከመንግሥት ባለሥልጣናት መግለጫዎችን እንጠብቃለን" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0