ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዩሪያ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና ለጎዴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ አኖሩ
13:45 02.10.2025 (የተሻሻለ: 13:54 02.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዩሪያ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና ለጎዴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ አኖሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዩሪያ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና ለጎዴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ አኖሩ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚያስገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ሲጠናቀቅ፤ ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎ ሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው አስነብበዋል።
በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ በሌላ በኩል ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው ተብሏል።
"እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንዱስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው። እድሎቻችንን የመጠቀም፣ ትብብሮችን የማጠናከር እና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳዩ ናቸው" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ ለእድገት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ