አርቲስት ፍሬሕይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአርቲስት ፍሬሕይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
አርቲስት ፍሬሕይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2025
ሰብስክራይብ

አርቲስት ፍሬሕይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

‎አንጋፋዋ ‎አርቲስትና ኮሜዲያን ጣልያን ሰፈር ከቀድሞ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በድንገተኛ ሕመም ሕይወቷ ማለፉን ስፑትኒክ አፍሪካ ከቅርብ የሙያ አጋሮቿ አረጋግጧል፡፡

“ጠዋት ገላዋን ታጥባ በተቀመጠችበት ድንገት ተዝለፍልፋ በመውደቋ ወደ ሕክምና ቦታ ለመውሰድ አምቡላንስ ቢጠራም ሕይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል” ብለዋል።

አርቲስቷ ‎የቀለጠው መንደርፎርፌረመጥነቃሸ የተሰኙትን ጨምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተሠሩ በርካታ ቴአትሮች ላይ ተውናለች።

‎ፍሬሕይወት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በውዝዋዜ እና ዳንስ ከተቀጠሩትና ችሎታቸውን በመድረክ ካሳዩት ከያንያን መካከል አንዷ ነበረች።

‎በበርካታ ፌልሞች፣ ድራማዎች እና የሙዚቃ ክሊፖች ላይም ሰርታለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0