ሩሲያ እና ኢራን ታሪካዊ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ፈጠሩ፤ ቁልፍ ስምምነቱ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ስትል ሞስኮ አስታውቃለች
11:29 02.10.2025 (የተሻሻለ: 11:34 02.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና ኢራን ታሪካዊ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ፈጠሩ፤ ቁልፍ ስምምነቱ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ስትል ሞስኮ አስታውቃለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ኢራን ታሪካዊ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ፈጠሩ፤ ቁልፍ ስምምነቱ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ስትል ሞስኮ አስታውቃለች
የተፈረመው የተቀናጀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ትብብር በሁሉም ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ዋና ዋና መመሪያዎችን የሚያስቀምጥ መሆኑን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ጥር 9 ሞስኮ ውስጥ በፑቲን እና በፔዜሽኪያን የተፈረመው ይህ ስምምነት፤ የሩሲያ እና የኢራን ከፍተኛ አመራር ወዳጃዊ ግንኙነቶችን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ምርጫ የሚያሳይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ውሉ ባለብዝኃ-ዋልታ የዓለም ሥርዓት እየተፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የተጠናከረ መስተጋብርን ያመጣል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
በዋና ዋና የባለብዙ ወገን ድርጅቶች ውስጥ ቅርብ ቅንጅት መፍጠር፣
ቀጣናዊ መረጋጋትን እና ደህንነትን ለማጠናከር የጋራ ጥረት ማድረግና
ለጋራ ተግዳሮቶች እና ስጋቶች የጋራ ምላሽ መስጠት።
ይህ ስምምነት እ.አ.አ. በ2001 ተፈረሞ ለ20 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን ስምምነት የሚተካ ይሆናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X