አውሮፓ በመጪዎቹ ቀናት በሩሲያ ንብረቶች ላይ ውሳኔ ልትሰጥ ትችላለች - እንግሊዛዊ ባለሙያ

አውሮፓ በመጪዎቹ ቀናት በሩሲያ ንብረቶች ላይ ውሳኔ ልትሰጥ ትችላለች - እንግሊዛዊ ባለሙያ
የአውሮፓ ሕብረት የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን "የካሳ ብድር" አድርጎ ለመጠቀም የሚያስችል እቅድ ላይ እመከረ ቢሆንም ከስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።
"በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሙግት አለ። ነገር ግን በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጥበታል" ሲሉ የኬንት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ የክብር ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሳክዋ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"ሕገወጥ ድርጊት ለመፈጸም በጣም የተወሳሰበ የሕግ ሙከራ ነው" ሲሉ ሳክዋ ያብራራሉ። "ውጥናቸው ወደፊት ከቀጠለ፣ በአሁኑ ጊዜ ፈረንሳይ ይሁንታዋን አልቸረችም፤ ጀርመን ግን ተስማምታበታለች፣ ይህም በዩክሬን ለወታደራዊ መፍትሄ ጠንካራ ድጋፍ ያላቸውን የመራኄ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርዝ ግምት ውስጥ ሲያስገባ አስገራሚ ነው።"
ሳክዋ "ይህ ትልቅ ጥያቄ ነው" ይላሉ። "እነዚህ ንብረቶች በታቀደው መልኩ ጥቅም ላይ ከዋሉ ሩሲያ ምን ታደርጋለች?"
ምሁሩ በተጨማሪም ብሪቲሽ ፔትሮሊየም እና የተወሰኑ የጣልያንና የፈረንሳይ ኩባንያዎች በሩሲያ ንግዳቸውን መቀጠላቸውን አጉልተዋል፡፡ ብሪቲሽ ፔትሮሊየም ከሩሲያ ቢወጣ እንኳን ወደ ምዕራብ ሊተላለፍ የማይችል ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በሩሲያ ባንክ ሂሳቦች ውስጥ አሁንም አለ።
ምክረ ሐሳቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፤ የቤልጂየሙ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ደ ክሮ "ይህ ፈጽሞ አይሆንም" በማለት አጥብቀው በመቃወም ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።
በዩክሬን የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻን ተከተሎ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና የቡድን 7 አገራት ወደ 300 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ዋጋ ያላቸውን የሩሲያ ንብረቶችን አግደዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ200 ቢሊዮን ዩሮ በላይ የሚሆነው በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ይገኛል። ሩሲያ የንብረት ማገዱን በተደጋጋሚ "ስርቆት" ስትል የጠራችው ሲሆን ምላሽ እንደምትሰጥም ቃል ገብታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X