የሴንት ኪትስና ኔቪስ ሚኒስትር ድህነትን እና የጤና ችግሮችን ከባርነት ተፅዕኖዎች ጋር አገናኙ

የሴንት ኪትስና ኔቪስ ሚኒስትር ድህነትን እና የጤና ችግሮችን ከባርነት ተፅዕኖዎች ጋር አገናኙ
ሴንት ኪትስና ኔቪስ እንደ ስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ መጠን ይስተዋሉባታል ሲሉ
የሴንት ኪትስና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ ፣ የኢኮኖሚ ልማትና ንግድ ሚኒስትር ዴንዚል ዳግላስ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ እነዚህ የጤና እክሎች በዘመናት ከዘለቀው ባርነት ከሚመነጩ ዘላቂ የማህበራዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች ጋር በህክምና የተገናኙ መሆናቸውን አስረድተዋል፤ ከእነዚህም መካከል ሥር የሰደደ ድህነት እና በቂ ያልሆነ የጤና እንክብካቤ ይገኙበታል።
ቅኝ ገዥዎች የካሪቢያን የንግድ ልማት ለትውልዶች እንዲንኮታኮት አድርገዋል፤ ምክንያቱም የቅኝ ግዛት ኢኮኖሚዎች አፍሪካውያንን ወደ እርሻዎች በኃይል በማጓጓዝ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው፣ ቅኝ ገዥዎችን ሲያበለጽጉ ለካሪቢያን ዘላቂ መዋቅር የሌለው ፍትሐሃዊነትን አስቀርተዋል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ዳግላስ እንዳሰምሩበት ፤ እንደ ሸንኮራ አገዳ ምርት ያሉ አካባቢያዊ ተፅዕኖ እና ለአየር ንብረት ለውጥ አስታዋፆ በማድረግ ላይ ያሉ ታሪካዊና ቀጣይነት ያላቸው ጉዳቶች ለካሳ ጥያቄዎች መነሻ ሆነዋል፤ ምክንያቱም ቅኝ ገዥ ኃይሎች በቂ ገንዘብ እያላቸው እንኳን ለቀጣናው የአየር ንብረት ችግሮች በበቂ ሁኔታ ምላሽ አልሰጡም።
ሴንት ኪትስና ኔቪስ "ገንዘብ ብቻ እየጠየቁ አይደለም" ያሉት ዳግላስ፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ የዕዳ ደረጃ በቀጥታ ከባርነት ውርስ የመነጨ መሆኑን እውቅና እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ የዕዳ ስረዛን እንደ ትርጉም ያለው የካሳ ፍትሕ አቅርበዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X