ባንኮች ሀብታሞችን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ሕዝብ ማገልገል አለባቸው ሲሉ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ሚኒስትሩ ተናገሩ
20:24 01.10.2025 (የተሻሻለ: 20:34 01.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱባንኮች ሀብታሞችን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ሕዝብ ማገልገል አለባቸው ሲሉ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ሚኒስትሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባንኮች ሀብታሞችን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ሕዝብ ማገልገል አለባቸው ሲሉ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ለሁሉም ሰዎች የተሻለ ተደራሽነት እንዲኖረው ማሻሻያ ያስፈልገዋል፤ ሲሉ የሴንት ኪትስና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ፣ የኢኮኖሚ ልማትና ንግድ ሚኒስትር ዴንዚል ዳግላስ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
ባንኮች ግለሰቦችን በኢንቨስትመንት ዙሪያ እንዲያስተምሩ፣ በአገር ውስጥ ንግዶች ላይ ኢንቨስት የማድረግ ዕድሎችን እንዲሰጡ እና የአነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ዕድገት እንዲደግፉ ጠይቀዋል። ይህም የሕዝብን ህልውና እና ብልጽግና ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ሲሉም ሞግተዋል።
ሚኒስትሩ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ እና እንደ ላቲን አሜሪካና ካሪቢያን ላሉ ሌሎች ክልሎችም የበለጠ ውክልና እንዲኖር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ለውጡን በተመለከተ አሁን የቀረቡት ሃሳቦች በቂ አይደሉም ሲሉም አክለዋል።
"ደቡብ ግሎባል ድምፅ ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁ። በጣም ጠንካራ ድምፅ፣ እናም የተለያዩ የደቡብ አባላት ውክልና የማግኘት እድል ሊሰጣቸው ይገባል፤ በተጨማሪም የፀጥታው ምክር ቤት እና ዛሬ የምንመለከተው የተመድ አካል ሆኖ እንዲሻሻል መርዳት አለባቸው።"
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X