ካሪቢያን እና አፍሪካ ተባብረው በሁለቱም ክልሎች ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ስኬትን እንደገና መገንባት አለባቸው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱካሪቢያን እና አፍሪካ ተባብረው በሁለቱም ክልሎች ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ስኬትን እንደገና መገንባት አለባቸው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ካሪቢያን እና አፍሪካ ተባብረው በሁለቱም ክልሎች ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ስኬትን እንደገና መገንባት አለባቸው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.10.2025
ሰብስክራይብ

ካሪቢያን እና አፍሪካ ተባብረው በሁለቱም ክልሎች ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ስኬትን እንደገና መገንባት አለባቸው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ

"ንግድ እንደ አፍሪካ እና ካሪቢያን ያሉ ሁለት ክልሎችን ዳግም የማዋሃድ እና የማበልጸግ ዋና አካል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን" ሲሉ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ፣ ኢኮኖሚ ልማት እና ንግድ ሚኒስትር ዴንዚል ዳግላስ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

አክለውም የጋራ መግባባትን እና የአካዳሚክ ስኬትን ለማሳደግ በአፍሪካ እና በካሪቢያን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የተማሪዎች ልውውጥ መርሃ ግብሮችን በማቅረብ፣ የትብብር መጨመር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በካሪቢያን እና በአፍሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር እንዲሁም በኪነ - ጥበብ እና በሥነ-ጽሑፍ ላይ ኢንቨስት በማድረግ የዘረኝነት አድሎ ያለበትን ትርክት ለማፍረስ ቁርጠኛ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

"ልጆቻችን ከልጅነታቸው ጀምሮ የመጻፍና የማንበብ፣ የሥራ እና የመተባበርን አስፈላጊነት እንደተገነዘቡ ማረጋገጥ አለብን። ይህም ጥቁር መሆን መጥፎ ነው፣ አፍሪካ ጨለማ ናት እንዲሁም የተወሰነ የቆዳ ቀለም ያላቸው ብቻ መሪዎች ናቸው የሚለውን አመለካከት ይለውጣል። ይህ መለወጥ አለበት፤ ይህንን ለውጥ አሁን ማስጀመር አለብን።"

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0