የሌቫንቲን ዝሆን ጥርስ የመጣው ከኢትዮጵያ እንጂ ከግብፅ እንዳልሆነ አዲስ ጥናት አረጋገጠ
19:09 01.10.2025 (የተሻሻለ: 19:14 01.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሌቫንቲን ዝሆን ጥርስ የመጣው ከኢትዮጵያ እንጂ ከግብፅ እንዳልሆነ አዲስ ጥናት አረጋገጠ
በደቡባዊ ሌቫንት ከ1600 እስከ 600 (አ.አ ከክርስቶስ ልደት በፊት) ይገበያይ የነበረው አብዛኛው የዝሆን ጥርስ ለረጅም ጊዜ ሲታመንበት እንደነበረው ከግብፅ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን አካባቢዎች ጋር ከተያያዙ የአፍሪካ ዝሆኖች የመጣ እንደነበር አዲስ ጥናት አመላከተ።
በሃይፋ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዋ ሓሬል ሾሓት የተመራው እና በጆርናል ኦፍ አርኪኦሎጂካል ሳይንስ የታተመው ይህ ጥናት፤ 624 የዝሆን ጥርስ ቅርሶችን በመተንተን 85% የሚሆኑት ከካርቱም በስተደቡብ ከስድስተኛው የዓባይ ወንዝ ዳር አካባቢ ከሚገኙ የአፍሪካ ዝሆኖች የተገኙ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ቀደም ሲል ግብፅ የዝሆን ጥርስ ንግድ ዋና ማዕከል ተደርጋ ብትታይም፣ ግኝቶቹ እንደሚያሳዩት ኑቢያውያንና ከኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት የንግድ መረቦችን በማስቀጠል ማዕከላዊ ሚና ተጫውተዋል። ይህ ሚናቸው በፖለቲካዊ ሁከት ወቅትም ቀጥሏል።
ጥናቱ የኢትዮጵያን በጥንታዊው ዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ቸል ተብሎ የነበረውን ሚና አጉልቶ አሳይቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X