ኬንያ ከውጭ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል 27.8 በመቶ ሲጨምር የኢትዮጵያ ደርሻ ከፍተኛ ነው ተባለ

ኬንያ ከውጭ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል 27.8 በመቶ ሲጨምር የኢትዮጵያ ደርሻ ከፍተኛ ነው ተባለ
የኬንያን የኢነርጂ እና ነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋቢ ያደረገው የሀገሪቱ ሚዲያ ዘገባ፤ የኤሌክትሪክ የገቢ ንግድ መጠን ከቀዳሚው ዓመት 1 ሺህ 199.80 ጊጋዋት ሰዓት ከነበረበት ወደ 1 ሺህ 533.85 ጊጋዋት ሰዓት ከፍ ብሏል፡፡ ይህም የ334.05 ጊጋዋት ሰዓት ጭማሪ አለው።
ይህ ጭማሪ ከኢትዮጵያ እና ከኬንያ ጋር የሚያገናኘው የ200 ሜጋዋት ከፍተኛ ቮልቴጅ ቀጥተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በታህሳስ 2023 ሥራ ከጀመረ በኋላ ያለውን የመጀመሪያውን ሙሉ ዓመት ያንፀባርቃል። በዘገባው የተካተቱ ተጨማሪ መረጃዎች
ኢትዮጵያ 1,274.42 ጊጋዋት ሰዓት በማቅረብ ኬንያ ከውጭ ከምትገዛው አጠቃላይ የኢሌክትሪክ ፍጆታ 83 በመቶውን ትይዛለች::
225.64 እና 33.79 ጊጋ ዋት ሰዓት በማቅረብ ኡጋንዳና ታንዛኒያ በቀደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡
ከኢትዮጵያ የሚገባው ኃይል ከሀገር ውስጥ የሙቀት ኃይል ማመንጫ የተሻለ ወጪ ቆጣቢ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ኬንያን በዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንድትቆጥብ አድርጓታል።
ሶዶ-ሞያሌ-ሱዋ የ500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር በሁለቱ አገራት መካከል የኃይል ዝውውርን የሚያስችል ሲሆን፣ ለቀጣዊ የኃይል ውህደት ወሳኝ አካል ተደርጎ ይታያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

