የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ሎጂስቲክስ ዘርፉን የበለጠ ለማዘመን የሚያግዝ የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቋሙ
15:50 01.10.2025 (የተሻሻለ: 16:04 01.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ሎጂስቲክስ ዘርፉን የበለጠ ለማዘመን የሚያግዝ የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቋሙ
የዘርፉን ችግር ይፈታል የተባለው ኮሜቴ የተዋቀወረው ላለፉት ሁለት ቀናት በጂቡቲ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የኢትዮ ጂቡቲ የቢዝነስ ማስፋፊያ ጉባዔ ተከትሎ ነው።
አዲስ አበባ የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ጉባኤ ክፍተቶችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የዳሰሰ እንደነበር ይታወሳል።
ኮሚቴው በሁለቱም ሀገራት ከሎጂስቲክስ ዘርፉ ጋር ትስስር ካላቸው ተቋማት የተውጣጣ ነው።
የዘርፉን ጤናማነት በመጠበቅ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በማስታጠቅ እና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ለሌሎችም ዘርፎች እንዲተርፍ ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ተጠቅሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia