ሩሲያ ወደ ናይጄሪያ የምትልከውን የስንዴ ምርት በ6 በመቶ ገደማ አሳደገች
14:34 01.10.2025 (የተሻሻለ: 14:44 01.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ወደ ናይጄሪያ የምትልከውን የስንዴ ምርት በ6 በመቶ ገደማ አሳደገች
በሩሲያ አግሮኤክስፖርት መግለጫ መሠረት፣ ሩሲያ እ.ኤ.አ.ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 21 ቀን 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ናይጄሪያ የላከችው የስንዴ መጠን 372 ሺህ ቶን ደርሷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው 352 ሺህ ቶን ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ አሳይቷል።
በ2024/25 የምርት ዓመት ናይጄሪያ ወደ አገር ውስጥ ያስገባችው ስንዴ መጠን ወደ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን ገደማ ደርሷል። ይህም ካለፈው ዓመት በ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን ብልጫ አለው።
ይህ ጭማሪ የተከሰተው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
🟠 ከፍተኛ ፍጆታ እና
🟠 ጊዜያዊ የአስመጪነት ቀረጥ ወደ ዜሮ መውረዱ ይጠቀሳሉ።
ከዚህ አጠቃላይ መጠን ውስጥ፣ የሩሲያ ስንዴ ድርሻ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ሲሆን፤ ይህም ቀደም ሲል በነበረው ዓመት ከተላከው መጠን ከሦስት እጥፍ በላይ ብልጫ አለው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X