የዛምቢያ ልዑካን በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ላይ ልምድ ለመቅሰም ያለመ ምክክር አደረጉ
13:59 01.10.2025 (የተሻሻለ: 14:04 01.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዛምቢያ ልዑካን በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ላይ ልምድ ለመቅሰም ያለመ ምክክር አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዛምቢያ ልዑካን በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ላይ ልምድ ለመቅሰም ያለመ ምክክር አደረጉ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በዲጅታል ኢትዮጵያ በተገኙ ውጤቶች እና በስትራቴጂው አመራር ላይ ገለፃ በማድረግ ኢትዮጵያ ወደ 2030 የሚወስዳትን ስትራቴጂ እየነደፈች መሆኑም አብራርተዋል።
አክለውም “የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ በአፍሪካ ሀገሮች መካከል ትብብር ሊኖር ይገባል” ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
የስማርት ዛምቢያ ኢኒሼቲቭ ብሔራዊ አስተባባሪና የዛምቢያ ልዑካን ቡድን መሪ ፐርሲ ቺኒያማ ኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ያደረገችውን ጉዞ አድንቀዋል፡፡
“በአፍሪካ ውስጥ ውጤታማ ነገሮች ስናይ ልምድን ከሌላ ቦታ ከመቅሰሙ ይልቅ ከዚሁ መቅሰሙ አንድ አይነት ዐውድ ውስጥ ስላለን ጠቀሜታው የጎላ ነው” ብለዋል፡፡
🪪 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንታወቀው፣ ልዑካኑ ከኢትዮጵያ ጋር በተለይ በዲጅታል መታወቂያ እና በአኅጉራዊ ዲጅታል ጉዳዮች ላይ በትብብሩ እንደሚሠሩ ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዛምቢያ ልዑካን በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ላይ ልምድ ለመቅሰም ያለመ ምክክር አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia
/