በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ
በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.10.2025
ሰብስክራይብ

በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ

የአረርቲ ከተማ ከንቲባ ተሻለ ጥላሁን “ከደረሰው ጉዳት አንጻር፣ ገና የተጎዱትን ለማዳን ጥረት እየተደረገ በመሆኑና መረጃው ከተለያዩ ማዕከላትና የሕክምና ቦታዎች የሚመጣ በመሆኑ የጉዳቱን መጠን በቁጥር ደረጃ ለመግለጽ ብቸገርም እጀግ አሳዛኝ ከባድ ጉዳት ደርሷል።” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“እስካሁን ባለኝ የተረጋገጠ መረጃ ከ30 በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥርም ከዚህ ቢበልጥ እንጂ አያንስም። አሁንም ገና የተጎዱትን ሰዎች የማውጣት ስራ እየተሠራና ተጎጂዎችን ለሕክምና ወደ አዳማ እና አዲስ አበባ እየላክን ነው። “

‎አደጋው የተከሰተው፣ ዛሬ 21/01/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓልን ለመታደም በተገኙ ምዕመናን ላይ ነው፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኘው ሕንጻ ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ‎ወቅት ለ”ፊኒሺንግ” የተረበረበ እንጨት ከጠዋቱ 1:45 ላይ መደርመስ አደጋውን ፈጥሯል፡፡

ከንቲባው ተሻለ “ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን የቤተክርስቲያኒቱን የግንባታ ሁኔታ ለመጎብኘት ረጅም ጊዜ ቆሞ ወደ ነበረው የእንጨት ርብራብ ላይ በመውጣቱ ነው ጉዳቱ የደረሰው። ርብራቡ ሙሉ በሙሉ ተደርምሷል።” ብለዋል፡፡

የሟቾች እና የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ከ30 በላይ ምእመናን ሕይወታቸው አለፈ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0